New Treaty on IP

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) አባል ሀገራት በአእምሯዊ ንብረት ፣ በጄኔቲክ ሃብት እና ተዛማጅ ማህበረሰባዊ እውቀት ላይ አዲስ ታሪካዊ ስምምነትን አፀደቁ፣ ኢትዮጵያም የመጨረሻውን ሰነድ /Final Act/ ፈርማለች።

WIPO Member States Adopt Historic New Treaty on Intellectual Property, Genetic Resources and Associated Traditional Knowledge, Ethiopia signed the Final Act.

*** *** *** *** ***

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) አባል ሀገራት እ.ኤ.አ ከሜይ 13-24 በጀኔቭ ባካሄዱት ዲፕሎማቲክ ኮንፍረንስ በአእምሯዊ ንብረት ፣ በጄኔቲክ ሀብቶች እና በተዛማጅ ባህላዊ እውቀት መብት ጥበቃ ላይ የተመሰረተ አዲስ አለምአቀፍ ስምምነትን በተባበረ ድምፅ አጽድቀዋል፡፡ ስምምነቱም የሁለት አስርተ አመታት አለም አቀፍ ጥረትና ተከታታይ ድርድርን በስኬት የቋጨ ታሪካዊ ምእራፍ ነው ተብሏል። የዚሁ አለም አቀፍ ስምምነት ድርድሮች እ.አ.አ በ1999 በኮሎምቢያ የቀረበውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ በዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) መሪነት እ.ኤ.አ በ2001 የተጀመሩ ሲሆን የማህበረሰቦችን የጄኔቲክና ሃገር በቀል እውቀት በአእምረዊ ንብረት ሥርዓት ጥበቃ የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ23 አመታት ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ኢትዮጵያም በድርድር ሂደቶቹ ከመሳተፍ ባሻገር በዚሁ የጄኔቲክ ሀብቶች እና በተዛማጅ ማህበረሰባዊ እውቀት ዲፕሎማቲክ ኮንፈረንስ ላይ ከመጀመሪያ አንስቶ በንቃት ተሳትፎ ያደረገች ሲሆን ሃገራችን ካላት ሰፊ የዘረመል ሃብቷ እና ባህላዊ እውቀቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችላትን አቋም ይዛለች። ስምምነቱን በማጽደቅና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የዲፐሎማቲክ ኮንፍረንሱ የስምምነት ማረጋገጫ የሆነውን የመጨረሻውን ሰነድ ሰነድ /Final Act ግንቦት 16/2016 ዓ.ም በልኡካን ቡድኑ መሪ ፈርማለች።

ይህ ታሪካዊ አለም አቀፍ ስምምነት በጄኔቲክ ሃብት እና በተዛማጅ ማህበረሰባዊ እውቀት ላይ ተመስርተው ለሚቀርቡ የፓተንት ማመልከቻዎች አመልካቾቹ የፈጠራዎቻቸውን የዘረመል ሀብቶች እና ተዛማጅ ማህበረሰባዊ እውቀቶች መገኛ ምንጭ እንዲገልጹ ያስገድዳል፡፡ በተጨማሪም የፓተንት ሥርዓቱን ውጤታማነት ፣ ግልጽነት እና ጥራትን ለማሳደግ እንደሚረዳና በዘረመል ሀብቶች እና ተያያዥ ባህላዊ እውቀት ላይ አዲስነት ወይም ፈጠራዊ ብቃት የሌላቸው ፈጠራዎች ያለአግባብ ዕውቅና እንዳያገኙ ለመከላከልም ያስችላል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል የመጨረሻውን ሰነድ የፈረሙት የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመሰል ኢትዮጵያ ስምምነቱን ስትፈርም የዘረመል ሀብቶችን እና ተያያዥ ባህላዊና ማህበረሰባዊ እውቀቶችን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን በኃላፊነት እና በፍትሃዊነት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ቀጣይ ሁኔታ በመገንዘብና በማለም ነው ብለዋል፡፡ አባል ሀገራት የጋራ ቅርሶቻቸውን ለማክበር እና ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት ስምምነቱ ይወክላል ፤ ይህም ለትውልድ የእውቀት እና የብልጽግና ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል ሲሉ አክለዋል። ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት መፈጸሟ ያላትን የበለፀገ የዘረመል ሀብቷን እና ባህላዊ እውቀቷን በመጠቀም፣ ሁሉም ማህበረሰቦች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ተገቢውን እውቅና እና ጥበቃ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም አያይዘው አብራርተዋል።

— — — — —

WIPO member states approved a ground-breaking new treaty on Intellectual property (IP), genetic resources, and associated traditional knowledge, on May 24th, 2024, marking a historic breakthrough that culminates decades of negotiations. These negotiations began at WIPO in 2001, following a proposal by Colombia in 1999. The discussions were notable for their inclusion of Indigenous Peoples and local communities.

Ethiopia actively participated from the beginning of the diplomatic conference, ensuring the treaty would benefit Ethiopia from its abundant genetic resources and traditional knowledge. Ethiopia has also signed the final Act of the treaty, signaling its intention to ratify and join the treaty to fully benefit from the provisions it offers.

The treaty mandates that when an invention in a patent application is based on genetic resources, traditional knowledge associated with genetic resources each contracting party shall require applicants to disclose the country of origin or source of these genetic resources and the Indigenous Peoples or local community that provided the traditional knowledge. The treaty aims to enhance the efficacy, transparency, and quality of the patent system, and to prevent patents from being erroneously granted for inventions that lack novelty or inventiveness with regard to genetic resources and associated traditional knowledge.

Ethiopian Intellectual property Authority Director General Mr. Woldu Yemessel, who signed the Final Act, affirmed that Ethiopia envision a future where genetic resources and traditional knowledge associated to genetic Resources are not only protected but also utilized responsibly and equitably. This treaty represents a collective effort to honor and preserve our shared heritage, ensuring that it remains a source of knowledge and prosperity for generations to come. He further elaborated that by committing to this treaty, Ethiopia aims to leverage its rich genetic resources and traditional knowledge, ensuring that all communities receive proper recognition and protection for their contributions.

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS