ቅጅ መብት ምንድን ነው?

የቅጅ መብት ማለት አንድን የአዕምሮ ውጤት የሆነን የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ-ጥበብ፣ የዕደ-ጥበብ፣ የኮምፒዩተር ኘሮግራም ወይም የፎቶግራፍ ሥራ ለሠራ ግለሰብ/ግለሰቦች የሚሰጥ መብት ሲሆን የተዛማጅ መብት ማለት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን የቅጅ መብት የሚያስገኙ የፈጠራ ሥራዎችን ተንተርሰው በሥራው ላይ የሚሳተፉ ከዋኞች፣ የድምፅ ሪከርዲንግ ኘሮዲውሰሮች እና የብሮድካስቲንግ ድርጅቶች የሚያገኙት መብት ነው፡፡ ማንኛውም የሥራ አመንጪ የሥራው ዓላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሥራው ወጥ (ኦርጅናል) ከሆነ እና ግዙፍነት ካገኘ ወይም ከተቀረፀ ሥራውን በማውጣቱ ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ ያገኛል፡፡ የፈጠራ ሥራውን የሰራ ግለሰብ ሥራውን የማባዛት፣ የመተርጎም፣ የማመሳሰል፣ የማቀናበር ወይም ወደ ሌላ አይነት የመቀየር፣በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦሪጅናል ሥራውን ወይም ቅጅውን የማከፋፈል፣ ኦሪጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለህዝብ የማሳየት መብት ይኖረዋል፡፡y..

ንግድ ምልክት ምንድን ነው?

ንግድ ምልክት ማለት የአንድን ሰው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡ ምልክቱም ቃላቶችን፣ ንድፎችን፣ ዲዛይኖችን፣ ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን ወይም የእነዚህን ቅንጅት ሊይዝ ይችላል፡፡ የንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ የአምራቹን ወይም የነጋዴውን መልካም ስምና ዝና ለመጠበቅ፣ በዕቃዎችና አገልግሎቶች መካከል መሳከርን ለማስወገድ፣ ነጻ ገበያን ለማበረታታት፣ የሸማቹን ጥቅም ለመጠበቅ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲዳብር ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ፓተንት ምንድን ነው?

ፓተንት ማለት ለአንድ አዲስ የፈጠራ ስራ ወይም ከዚህ በፊት በነበረ ፈጠራ ላይ ለተሰራ አዲስ የማሻሻያ የፈጠራ ስራ የሚሰጥ መብት ሲሆን መብቱ ለተወሰነ ጊዜ የሚያገለግልና ለባለፓተንቱ ብቸኛ መብት የሚያጎናጽፍ ህጋዊ የጥበቃ መብት ነው፡፡ ባለፓተንቱ ፓተንት ያገኘበትን የፈጠራ ስራ ለማከራየት፤ ለመሸጥ ፤ በዉርስ ለማስተላለፍ፤ በሱ ለመገልገል ወይም በሌላ በማናቸዉም መንገድ ለመጠቀም ህጋዊ መብት የሚኖረው ሲሆን ለፈጠራው የተሰጠዉ የጥበቃ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ ሶስተኛ ወገኖች ከባለፓተንቱ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር ፓተንት የተሰጠበትን ፈጠራ መጠቀም አይችሉም፡፡

Recent posts
Director General meets Israel Embassy Representative
20 Dec 2022

The Ethiopian Intellectual Property Authority (EIPA) Director General, Ermias Yemanebirhan (PhD) meets Mr. Alon Roth, Especially Council of Israel Embassy...

Read More
Bilateral Agreement Signed
08 Dec 2022

The Authority signed a bilateral memorandum of understanding with Steam Power Ethiopia on December 08/2022, in Addis Ababa having the...

Read More
በመልክዓ ምድር አመልካች ምርቶች ፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
17 Nov 2022

በመልክዓ ምድር አመልካች ምርቶች ፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የመልክዓ ምድር አመልካች ምርቶች ፕሮጀክትን በበላይነት ከሚያስተባብረው የፈረንሳይ...

Read More
ኢትዮጵያ የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት በሚያዘጋጀው የሃገራት የኢኖቭሽን መለኪያ ከፍተኛ እመርታ ማሳየቷ ተመላከተ
10 Oct 2022

ኢትዮጵያ በ2022ቱ የዓለም የአእምሯዊ ንብረት ድርጅት የሃገራት የኢኖቬሽን ደረጃ መለኪያ በ2020 ከነበረችበት የ127ኛ ደረጃ እና በ2021 ከነበረችበት የ126ኛ ደረጃ አስራ...

Read More
የባህላዊ ሕክምናን በአእምሯዊ ንብረት ስርዓት በማስጠበቅ የገበያ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እንደሚቻል ተገለጸ
07 Oct 2022

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት በመተባበር የባሕላዊ ሕክምናን በአእምሯዊ ንብረት ስርዓት በማስጠበቅ ባሕላዊ ሐኪሞች...

Read More
የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማትን ለማጠናከር ተደራሽነቱን ማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንዳለው ተገለጸ
04 Oct 2022

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮዎች በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ መስከረም 23/2015 ዓ.ም ውይይት አደረገ፡፡ የባለስልጣን...

Read More
Contact Info

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
FAX :-  +251 115 52 92 99
25322/1000

Usefull Links
Location