የኬቢ አካዳሚ ተማሪዎች በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የኬቢ አካዳሚ ተማሪዎች በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ፡፡ በጉብኝቱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በአእምሯዊ ንብረት ምንነትና ጥበቃ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የአእምሯዊ ንብረት ዘርፎች ምዝገባ ሂደቶችንም በሥራ ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ታዳጊዎች ለፈጠራ ሥራ ዝንባሌ እንዲኖራቸው፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስራዎች ተሳትፎአቸው እንዲዳብር ማበረታታትና የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ እንዲኖራችው ማድረግ ወደ ፊት በዘርፉ ለሚኖራው ሚና ግብዓት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ትምህርታዊ ጉብኝቱ ተማሪዎች ለፈጠራ ስራዎችና አእምሯዊ ንብረት ዘርፎች ጥበቃ ግንዛቤና ፍላጎት እንዲኖራቸው ማድረጉን አስተባባሪ መምህራኖች ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ከአስተባባሪ መምህራኖች ጋር በተካሄደው ውይይት ኬቢ ኮሌጅ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ድጋፍ ማዕከል ስራዎች ተሳትፎ እንዲኖረው የጋራ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS