የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማትን ለማጠናከር ተደራሽነቱን ማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንዳለው ተገለጸ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮዎች በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ መስከረም 23/2015 ዓ.ም ውይይት አደረገ፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር እንዳለው ሞሲሳ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማትን ለማጠናከር ሶስት ዋና ዋና አዋጆችን የፈጠራ የአነስተኛ ፈጠራና የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ፣ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጆች በማውጣት እና ማሻሻያ ህጎችንም በማውጣት ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ውጤታማ እና ተደራሽ ስራዎችን ለመስራት ከባለድርሻዎች ጋር በትብብር መስራቱ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው አስምረውበታል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የ2014 በጀት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015 በጋራ የሚሰሩ ስራዎችን ዕቅድ አስመልክቶ የባለስልጣኑ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ወንድወሰን ግዛቸው የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮዎች የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀማቸውን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅዶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዕቅዶቻቸው ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር ተጣጥሞ እንዲዘጋጅ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በቅንጅት የሚከናወኑ ስራዎችን በማሳደግ የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባና ጥበቃን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም ለፈጠራ ባለሙያዎች ተደራሽ በማድረግና የዘርፉን ግንዛቤ በማሳደግ የአእምሯዊ ንብረት የባለቤትነት መብት እንዲያገኙ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ ይህንንም አውን ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማንኛውንም የቴክኒክ ድጋፍና ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS