የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የጽ/ቤታችን አጋር ምህረትአብ ልዑል እና ጓደኞቹ …

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የጽ/ቤታችን አጋር ምህረትአብ ልዑል እና ጓደኞቹ የህግ ቢሮ ድጋፍ አደረገ

22/07/2012

ጽ/ቤታችን ድጋፍ በጠየቀበት ወቅት በሙሉ ያለማቅማማት ቀና ምላሽ ሲሰጡ የነበሩት አጋር አካላትና የንግድ ምልክት ወኪሎች አሁንም በሀገራችን የተጋረጠውን የኖብል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) አለም አቀፍ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ድጋፍ ለሚፈልጉ ዜጎቻችን እርዳታ ለማሰባሰብ በምክትል ዋና ዳይሬክተር የሚመራ ኮሚቴ አደራጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የጽ/ቤታችን አጋር የሆነው ምህረትአብ ልዑል እና ጓደኞቹ የሕግ ቢሮ የኖብል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19)ን ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል አቅም ለሌላቸው ዜጎች የሚሆን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ ያደረገ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ተባብረን የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19)ን ስርጭት እንግታ!!!

እራስዎን ይጠብቁ!

ወገንዎን የጠብቁ!

CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS