ኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር “የዳያስፖራው ሚና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን” በሚል መሪ ሃሳብ ጥር 5/2014 ዓ.ም ምክክር አካሄደ፡፡
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ የምታደርገውን ርብርብ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ተደግፎ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት የዲያስፖራው አባላት ድጋፍ አዎንታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምር ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የግልና የመንግስት ተቋማት አዳዲስ ግኝቶቻቸውንና የምርምር ውጤቶቻቸውን ወደ ኢንቨስትመንት አማራጮች ለማሸጋገር ከዳያስፖራው ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል ፎረም መቋቋሙ ተገልጿል፡፡