የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከአውሮፓ ፓተንት ቢሮ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመሰል በጄኔቫ እየተካሄደ ካለው 68ኛው የአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ሐምሌ 2/2018 ዓ.ም ከአውሮፓ ፓተንት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች ጋራ ባካሄዱት ውይይት ባለፉት አራት አመታት በላይ በሁለቱም ተቋማት መካከል ሲከናወኑ የቆዩ የትብብር ፕሮግራሞች ውጤታማ እንደነበሩ አረጋግጠዋል፡፡ በዚህ ረገድ የፈጠራና አነስተኛ ፈጠራ (ፓትንት) አዋጅ በማሻሻል ሂደት፤ የፓተንት ምርመራ የስራ መመሪያ በማዘጋጅትና በሀገራዊ ቋንቋ እንዲተረጎም በማድረግ እንዲሁም የሀገራችን አስር ዩኒቨስትሪዎች የምርምር መረጃዎችን በነፃ የሚያገኙበት/PATLib/ ስርዓት በመፍጠር የተደረጉ ድጋፎች አበራታች መሆናቸውም በውይይቱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከአውሮፓ ፓተንት ቢሮ ጋር የጀመረውን የስራ ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ የጠቀሱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በተለይም ኢትዮጵያ በቅርቡ የፓሪስ ህብረት/Paris Convention/ አባል በመሆነዋና የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገቸው ባለው ድርድር ሰፊ ልምድ የሚፈልግ በመሆኑ የአውሮፓ ፓተንት ቢሮ ድጋፍና ትብብርን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ የአውሮፓ ፓትንት ቢሮ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የፕሬዚዳንቱ ዋና አማካሪ ማሪያና ካሬፖቫ በበኩላቸው መ/ቤታቸው ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ጋር የጀመረውን የድጋፍና ትብብር ግንኙነት በተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS