የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) በየዓመቱ በሚያወጣው የኩባንያዎች ኃብት መለኪያ (Global Innovation Index) ከአፍሪካ https://www.wipo.int/gii-ranking/en/ethiopia/section/innovation-top-performers የኢትዮጵያ አየር መንገድን በ2026 ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የላቀ የብራንድ ዋጋ ካላቸው ተርታ በመመደብ የብራንድ ዋጋው(Brand Value) 323.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱ መላውን የሀገራችንን ሕዝብና የአየር መንገዱን ታታሪ ሠራተኞች ታላቅ ኩራትና ደስታን የሚፈጥር ታሪካዊ ስኬት ነው! ላስመዘገባችሁት አስደናቂ ውጤት ለመላው የአየር መንገዱ ማኔጅመንት፣ የበረራ ባለሙያዎች፣ የቴክኒክ ቡድን እና መላው ሠራተኞች በሙሉ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ሠራተኞችና አመራሮች ልባዊ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያጋጥሙ የኢኮኖሚና የገበያ መናወጦችን በጽናት በመቋቋም፣ የበረራ መዳረሻዎቹን በማስፋፋት እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ወደ አገልግሎት በማስገባት ረገድ የፈጠረው ተዓምር ለሌሎች የአፍሪካ ተቋማት ትልቅ አርዓያ ነው። ከዚህም በላይ ይህ ስኬት የአገልግሎት ጥራትን ማዕከል ያደረገ ደንበኛ ተኮር አሠራር ውጤት መሆኑ አያጠራጥርም። ደንበኞች በአየር መንገዱ ላይ ያላቸው እምነት እያደገ መምጣቱ ለብራንድ ዋጋው ከፍተኛ መሆን ዋነኛው መሠረት ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስመዘገበው ይህ የ323.9 ሚሊዮን ዶላር ከፍተኛ የብራንድ ዋጋ (Brand Value) ለራሱ ከተረፈው ስኬት ባለፈ፣ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለአፍሪካ ኩባንያዎችና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሥነ-ምህዳር ያለው በጎ ተጽዕኖ እና ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ሌሎች ሀገር በቀል ኩባንያዎች ይህንን አርዓያነት በመከተል አገልግሎቶቻቸውንና ምርቶቻቸውን ከፍተኛ ጥራት የተላበሰ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገዘፈ ብራንድ ባለቤት እንዲሆኑ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ይመክራል፡፡ በድጋሚ ለመላው የአየር መንገዱ ሠራተኞች፣ አመራሮችና ባለድርሻዎች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡