የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ የፊርማ ስነ-ስርኣት ተካሄደ

የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ የፊርማ ስነ-ስርኣት ተካሄደ———————————-ኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍን በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ መግባቱን ዋና ዳይሬክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን ከክፍል ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ነሃሴ 5/2013 ዓ.ም ባደረጉት የዕቅድ መፈራረም ስነ-ስርዓት ላይ ገልጸዋል፡፡የክፍል ኃላፊዎች በዕቅዳቸው ላይ የተካተቱ ተግባራትን በአግባቡና በወቅቱ በመተግበር ለጽ/ቤቱ ተገልጋዮች የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጻል፡፡ ለዚህም ኃላፊዎች ክፍላቸውን በአግባቡ በመምራትና ለውጤት በመስራት የተጣለባቸውን ኃላፊነት መውጣት እንደሚገባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡በዕቅዱ ላይ የተካተቱ ተግባራትን በከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ወጪ ቆጣቢ፣ በከፍተኛ ጥራትና ባነሰ ጊዜ በመፈጸም የዕቅድ አፈጻጸም ደረጃን ማሳደግና ለተገልጋዮች የላቀ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም አቶ ኤርሚያስ ተናግረዋል፡፡ የማናጅመንት አባላት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶቻቸውን የዕቅድ፣ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በወቅቱ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዳሉ ሞሲሳ የ2013 በጀት ዓመት መልካም አፈጻጸሞችንና ተሞክሮችን በማጠናከርና የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የክፍል ኃላፊዎች የተፈራረሙትን የዕቅድ ሰነድ በየደረጃው ለቡድን መሪና ለፈጻሚ ካስኬድ በማድረግ በ2014 በጀት ዓመት የጽ/ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመንና ማሻሻል ይገባል፤ ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ቡድን መሪዎች ከክፍል ኃላፊዎች ጋር ዕቅድ የመፈራረም መርሃ ግብር በቀጣይ ሳምንት የሚካሄድ በመሆኑ የዝግጅት ስራ እንዲያጠናቅቁ ለማናጅመንት አባላት አክለው ገልጸዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS