የአቅመ ደካማ ዜጋ መኖሪያ ቤት ተገንብቶ ለባለቤቱ የማስተላለፍ መር-ግብር ተካሄደ

የአቅመ ደካማ ዜጋ መኖሪያ ቤት ተገንብቶ ለባለቤቱ የማስተላለፍ መር-ግብር ተካሄደ

==========+==========

የኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግና ተጠሪ ተቋማት በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ የአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት እድሳት አስጀምረው ግንባታቸው በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ዛሬ ረቡዕ ጳጉሜ 3/2013 ዓ.ም የመልካምነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ተገለጸ፡፡ በጠቅላይ አቃቤ ህግና በተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች የገንዘብ መዋጮ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በመታደስ ላይ ከሚገኙ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶች መካከል የአቶ ምንዳዬ ዘነበ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት የርክክብ መርሃ ግብር ተካሄዷል፡፡

አቶ ምንዳዬ ደካማ፣ ያረጀና ከደጅ የማይሻል መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶ በአዲስ መልክ በመገንባቱ የተሰማቸውን ደስታ በመርሃ ግብሩ ላይ ገልጸዋል፡፡ ከመኖሪያ ቤቱ እድሳት በተጨማሪ መኖሪያ ቤታቸው በወለል ምንጣፍና በሶፋ እንዲያምር ከመደረጉም በላይ የፍራሽ እና የአልባሳት ድጋፍም እንደተደረገላቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ በመገንባት ላይ የሚገኙና አዲስ የኮንትራት ውል የሚገባላቸው የአቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች እድሳትና ግንባታ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ የሚተላለፍ እንደሚሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ አአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ሰራተኞች እና የሌሎች ተቁዋማት ሰራተኞች ለአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት አድሳትና ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS