ኢትዮጵያ በ2022ቱ የዓለም የአእምሯዊ ንብረት ድርጅት የሃገራት የኢኖቬሽን ደረጃ መለኪያ በ2020 ከነበረችበት የ127ኛ ደረጃ እና በ2021 ከነበረችበት የ126ኛ ደረጃ አስራ አንድ ደረጃዎችን በማሻሻል 117ኛ ደረጃን መያዝ ችላለች፡፡

ይህ መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ የሃገራትን የኢኮኖሚ ደረጃ መሰረት በማድረግ በተደረገ ትንተና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው 12 ሃገራት መካከል የ3ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ 80 የመለኪያ መስፈርቶችን በመጠቀም የሃገራቱን የኢኖቬሽን ደረጃ የሚለካው ይህ መረጃ ከሳህራ በታች ካሉ 46 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ 14ኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ደረጃቸውን ካሻሻሉ 16 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ከፍተኛ እመርታን ከስመዘገቡት አንዷ መሆኗን ጠቁሟል፡፡

ይኸው መረጃ ስዊዘርላንድን፣ አሜሪካን እና ስዊድንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን ቻይና 11ኛ፣ እስራኤል 16ኛ እንዲሁም ህንድ የ40ኛ ደረጃ መያዛቸውን አስቀምጧል፡፡