ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ መንፈቅ ዓመት ዕቅደ አፈጻጸም ጥር 25/2014 ዓ.ም ገመገመ፡፡
የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ወንድወሰን ግዛቸው በበጀት ዓመቱ በዝግጅትና በትግበራ ምዕራፎች የተከናወኑ የቁልፍና አበይት ተግባራት በማስመልከት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ባለስለጣን መስሪያ ቤቱ በዝግጅት ምዕራፍ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል አሳታፊ ዕቅድ በማቀድ ወደ ትግበራ መገባቱ፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ለአቅመ ደካማ ዜጎች የቤት እድሳት፣ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት፣ ለሀገር መከላከያ እና ለተፈናቀይ ወገኖች ተሳትፎና ድጋፍ ማድረጋቸውን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
በትግበራ ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት፣ በህግ ተፈጻሚነትና በቅንጅታዊ አሰራር እና በአሰራር ስርዓት ግንባታና በጀት አጠቃቀም የትኩረት መስክ አንጻር ግምገማ ተደርጓል፡፡
በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ረገድ በንግድ ምልክት 1536፣ በቅጅ መብት 317 እንዲሁም በፓተንት 81 በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 1934 የፈጠራ ባለመብቶች የባለቤትነት መብት ማግኘታቸውን ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን በንግድ ምልክት፣ በፓተንት እና በቅጅ መብት ዘርፎች ለሰጣቸው የምዝገባና ተያያዥ አገልግሎቶች 12,049,314 ለመሰብሰብ አቅዶ 12,616,890.60 ብር በመሰብሰብ ለመንግስት ፈሰስ ማድረጉን በሪፖርቱ ተገልጸል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚሰጠው የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ አገልግሎት ቅሬታ ያለው ማንኛውም ደንበኛ ጉዳዩን ለአእምሯዊ ንብረት ትሪቡናል ይግባኝ ማቅረብ እንደሚቻል በተዘረጋው ስርዓት መሰረት 37 የይግባኝ አቤቱታዎች በመቀበል፣ 29 ችሎት በማስቻል፣ 25 የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ በ18ቱ ይግባኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መሰጠቱ ተብራርቷል፡፡