በቴክኖሎጂ መረጃዎችና በኢኖቬሽን ስርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ

በቴክኖሎጂ መረጃዎችና በኢኖቬሽን ስርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ

===================

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዩኒቨርሲቲዎችና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተለያዩ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ቢጠቀሙ ለምርምርና ስርጸት እንዲሁም ለአዳዲስ የምርምር ስራዎቻቸው ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ በተቋማት ትስስር ፖሊሲ፣ በፈጠራ ስራዎች አስተዳደር እና አእምሯዊ ንብረት አያያዝ ነሐሴ 28-29/2013 ዓ/ም በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው ላይ በክላስተር አንድ ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ ትስስር ኃላፊዎች እና ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል፡፡

ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የቴክኖሎጂና ኢኖቨሸን ድጋፍ ማዕከል አስተባባሪ ጳውሎስ ዳዊት ስለ ቴክኖሎጂና ኢኖቨሸን ድጋፍ ማዕከል ፕሮጀክት ዓላማ፣ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊስ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደቶችንና የአእምሯዊ ንብረት ማኔጅመንት ጋር በተያያዘ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS