የፈጠራ ባለሙያ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

ጸሃፊ- ዶ/ር አማንዳ ጄን ጆርጅ

በሲኪው ዩንቨርስቲ አውስትራሊያ የቢዝነስ እና ህግ ትምህርት ቤት የድህረ ምረቃ ጥናት አስተባባሪ፤ በኢኖቬሽን እና አእምሯዊ ንብረት ህግ ከፍተኛ ሌክቸር

ትርጉም፡ ስንታየሁ ታደሰ

አርታኢ፡ ብሩክ ወርቅነህ

የፈጠራ ባልሙያዎችን አእምሯዊ ንብረት ለመጠበቅ የተነደፈው የፓተንት ሕግ የፈጠራ ባለሙያዎች ሰዎች እንደሆኑ በማሰብ ሲሆን ፣ “ፈጠራዊ ብቃትን” እንደ አንድ ነገርን በአዲስ መንገድ መተግበርን – በተመሳሳይ ጥበብ ውስጥ ላለ ባለሙያ ግልፅ አለመሆኑን በመውሰድ ነው።  

ይሁንና ሳምንት በጉዳዩ በዓለም  የመጀመሪያው ዳኝነት የአውስትራሊያ ፌደራል ፍርድ ቤት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓት የፈጠራ ባለሙያ ተብሎ እንዲጠራ ውሳኔ አስተላልፏል።

አሜሪካዊው ሳይንቲስት ስቴፈን ታለር በዘረጋው DABUS (Device for Autonomous Boot Strapping of Unified Sentence) በተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓት ፈጠራዎችን በፓተንት ማስመዝገብ እንደማይችል የሀገሪቱ የፓተንት ኮሚሽነር ያስተላለፈውን ውሳኔ ፍርድ ቤቱ ሽሮታል/ቀልብሶታል፡፡

DABUS ኩርባ ቅርፅ ያለው ዘመናዊ የሙቀት ማስተላለፊያ እና መያዣ እንዲሁም ለድንገተኛ ጊዜ የሚያገለግል ብልጭ ድርግም የሚል ብርሃን/መብራት የለው ምርት በራሱ ንድፉን እንደሰራ ታለር ተናግሯል፡፡ ስለሆነም ታለር ያደረግኩት አስተዋይ ባለመኖሩ የፈጠራው ባለመብት መሆን አይገባኝም ይላል፡፡

በዓለም አቀፍ የፓተንት ትብብር ስምምነት በተፈቀደው መሰረት በ17 ሀገራት ውስጥ የፓተንት ማመልከቻዎች አስገብቷል። በአሜሪካን፣ በእንግሊዝ፣ በጀርመን፣ በአውሮፓ እና በአውስትራሊያ ፓተንት ቢሮዎች ተቀባይነት አላገኝም። በሌሎች 11 ሀገሮች ውስጥ ደግሞ የፓተንት ጽ/ቤት ውሳኔዎች በመጠበቅ ላይ ነው።

አንድ የፓተንት ጽ/ቤት እርሱም የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች እና የአእምሯዊ ንብረት ኮሚሽን የታለርን ፓተንት የአውስትራሊያው ፌደራል ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ ከሁለት ቀናት በፊት ፓተንቱን አጽድቆታል፡፡

ስለዚህ አውስትራሊያ ማሽንን እንደ የፈጠራ ባለሙያ እንዲሰየም የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አይደለችም። ነገር ግን የደቡብ አፍሪካ ፓተንት ጽ/ቤት አሰራር የፈጠራ ባለመብትነትና ባለቤትነትን ጣምራ ምርመራ ስለሚከለክል የፓተንት መብቱን ሊሰጥ ችሏል፡፡ 

በዚህም መሰረት ታለር የፓተንት ኮሚሽነሩን ውሳኔ ባለመቀበል ይግባኝ የጠየቀበትና ለፈጠራ ስራው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንሱ የፓተንት ባለቤትነት መብት እንዲያገኝ የፌደራል ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ በዓለም የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ማሽን መፍጠር ይችላል፣ ግን የፈጠራውን ባለቤት መሆን አይችልም

አብዛኞቹ የፓተንት ቢሮዎች የታለር ማመልከቻን ውድቅ ያደረጉበት ውስን ምክንያቶች እንደ ህጉ አፃፃፍ እና የፓተንት ኃላፊዎች የህጎቹ አረዳድ ይለያያሉ።

ይሁንና አንዳንድ የተለመዱ ጭብጦች አሉ፤ ለአብነት በእንግሊዝ እና በአውስትራሊያ ፓተንት ቢሮዎች ውስጥ ዋናው መሰናክል መርማሪዎቹ ማሽን አንድን ነገር መፍጠር ይችላል የሚለውን እሳቤ አለመቀበላቸው ሳይሆን አንድ ማሽን የፈለሰፈውን እንዴት ባለቤት ሊሆን እንደሚችል ማየት አለመቻላቸው ነበር።

ይህ የባለቤትነት ጉዳይ ለፓተንት ሂደት አስፈላጊ ነው። አመልካቹ ከፈጠራ ባልሙያው የተለየ በሚሆንበት ግዜ አመልካቹ ከፈጠራ ባለሙያው የባለቤትነት ወይም ውክልና በትክክል ማግኘታችውን እንዲያሳዩ ይጠይቃል።

የፓተንት ጽ/ቤቶች የታለር ማመልከቻን በዳቡስ/ DABUS መሠረት፣ እንደማሽን የባለቤትነትን መብት መያዝ ወይም ለታለር ማስተላለፍ ስላልቻለ፣ ፈጠራውን ባለመስራቱ ራሱን እንደ ፈጠራ ባለሙያ ለመሰየም ባለመፈለጉ ውድቅ አድርገውታል። 

የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ፓተንት ጽ/ቤቶች የየራሳቸው የፓተንት ህጎች የፈጠራ ባለሙያ ሰው መሆን እንዳለበት ሃሳብ እንደሚያቀርብ ተከራክረዋል። የአሜሪካ እና የአውሮፓ ቢሮዎችም ይህንን ክርክር አቅርበዋል።

የአውስትራሊያ ፌደራል ፍርድ ቤት ለምን ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፈረደ

ይሁንና ይህ ጉዳይ ወደ አውስትራሊያ በመጣበት ወቅት የሀገሪቱ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ ዮናታን ቢች ለማሽኑ የወገነ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በአውስትራሊያ ፓተንት ኮሚሽነር የተሰራውን ትርጓሜ በመገልበጥ ዳኛ ቢች የፓተንት ህጉ የፈጠራ ባለሙያው የባለቤትነት መብቱን እንዲይዝ ወይም ለአመልካቹ እንዲያስተላልፍ አያስገድድም ብለዋል። በቀላሉ አመልካቹ ህጉ እውቅና እንደሚሰጠው የፈጠራውን ባለቤትነት መብት እንዲቀበል የሚጠይቅ ነበር – ለምሳሌ ልክ የወተት ሀብት ልማት አርሶ አደር የላሞቹን ወተት ባለቤትነት መብት እንደሚቀበለው።

ታለር የባልቤትነት መብቱን የተቀበለው የዳቡስ/ DABUS ባለቤት በመሆኑ እና የእሱን ኮድና ውጤት ፈተራውን ጨምሮ ስለሚቆጣጠር ነው።

ዳኛ ቢች የእሱ ትሩጓሜ የፓተንት ህግን መስረት ያደረገ የፈጠራ ስራን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቅሷል። ይህን አመለካከት ሳይወስዱ የሚመጣው “እንግዳ ውጤት” የዳቡስ/ DABUS ፈጠራ ባለቤት የሌለው እና ፓተንት የማያሰጥ መሆኑ ይሆናል። ስለዚህ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፈጠራዎች ፓተንት ጥቁር ቀዳዳ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን የመቆጣጠር ፍርሃቶች

ለአሁን የዳኛ ቢች ውሳኔ ማለት አውስትራሊያ እና ደቡብ አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እንደ የፈጠራ ባለሙያ የሚቀበሉ ሁለት አገሮች ብቻ ናቸው ማለት ነው።

የእንግሊዝ የህግ ተግዳሮት ውጤት ላይ በመመስረት የታለር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን ተቃውሞ ለረጅም ግዜ የግድ አይሆንም። የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በጥቅምት ወር በይግባኙ ላይ ውሳኔ ይሰጣል። ታለር በአሜሪካን ፓተንት እና ንግድ ምልክት ጽ/ቤት እና በአውሮፓ ፓተንት ጽ/ቤት ውሳኔዎችን ይግባኝ በማለት ላይ ይገኛል።

ሌሎች ፍርድ ቤቶች ከዳኛ ቢች በተለየ መንገድ ከወሰኑ፣ አውስትራሊያ እና ደቡብ አፍሪካ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለተፈለሰፉ ፓተንቶች ለጊዜው እንደ ምልክት ይሆናሉ ማለት ነው። ይህም ፓተንት ያላቸውን የውጭ ፈጠራዎች ለመጠቀም የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የበለጠ እንዲከፍሉ ሊተው ይችላል።

ግን ሌሎች ህጋዊ ውሳኔ ሰጪዎች የአውስትራሊያን መንገድ ቢከተሉስ?

የሜልበርን የህግ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ባልደረባ ማርክ ሳንፊልድ እንዳስጠነቀቀው ማሽኖችን እንደ ፈጠራ ባለሙያ መቀበል “በአውቶሜሽን ፓተንት ማመንጫዎች” ቴክኖሎጂን በብቸኝነት መያዝ በጣም በብዛት ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።

ይህ እንደ ጎግል፣ አፕል፣ ፌስቡክ፣ አማዞን እና አሊባባ ያሉ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በጣም ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የበላይነት የበለጠ ያሰፋል። የኮርክ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኢኮኖሚስት ዊም ናውዴ እንደፃፈው፣ እነዚህ መድረኮች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውስጥ እነሱን ወደ ብቸኛ ባለቤት እና ጠባቂነት መለወጥ ትልቅ የመጀመሪያ ጀማሪ ጠቀሜታ አላቸው። 

ሰመርፊልድ ይህንን ለመከላከል ፈጠራን ለሰው ልጅ ጽንሰ-ሀሳብ መገደብ “ዋናው የህግ እንቅፋት” ነው ሲል ተከራክሯል።

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS