በፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጠ

በፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጠ

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የፈጠራ ስራዎች ውድድር በማካሄድ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ የሆነው ናትናኤል በሃይሉ “Rotational Laser CNC Machine” በመፍጠሩ በአንደኛ ደረጃ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ተማሪው የሰራው የፈጠራ ስራ በተለያዩ ክብ ቅርጽ ባላቸው እንደ ቀርቅሃ፣ አልሙኒየም፣ ፕላስቲኮችና እንጨቶችን በማሽከርከር እያቃጠለ የተለያዩ ዲዛይኖችን ማተም የሚያስችልና ለበርካታ ዓመታት የታተመው ዲዛይን ሳይበላሽ እንዲቆይ የሚያደርግ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት የሚውል ደረጃ የሚወጣ ዊልቸር በመስራት የሁለተኛ ደረጃን ያገኘችው ተማሪ አፍራህ ሁሴን ስትሆን ምርቱ ወደ ተግባር ሲገባ አሁን በየተቋማቱ እና በተለያዩ ቦታዎች አካል ጉዳተኞች ደረጃ ለመውጣት የሚቸገሩበትን መፍትሄ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሙኖረው ተገልጿል፡፡

“Coffee bean Separator machine” በመስራት የሶስተኛ ደረጃን ያገኙት አንተነህ በቀለ፣ ሜሮን ጎንፋ እና ቃልኪዳን የቡድን የፈጠራ ስራ ሲሆን ጥራት ያላቸውን እና የሌላቸውን የቡና ፍሬዎች በቀለማቸው መለየት የሚያስችል እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ደረጃ አሸናፊ ለሆኑ የፈጠራ ባለመብቶች የኢንተርፕርነርሺፕ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎቻቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥና ወደ ገበያው ለመግባት የሚያስችላቸውን የቢዝነስ ዕቅድ አዘገጃጀት ስልጠና እንደሚያመቻችላቸው በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ አሸናፊ ለሆኑ የፈጠራ ባለመብቶች የማበረታቻ የሞባይል ሽልማት ያበረከተ ሲሆን በቀጣይም ከወጣቶች ጋር እንደሚሰራ የተቋሙ ተወካይ ገልጸዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS