Consultation workshop on draft GI law

Consultation workshop held on the draft GI law

Experts from the Ethiopian Intellectual Property Authority, the Ministry of Innovation and Technology, Jimma University, the Ethiopian Coffee and Tea Authority, the Ethiopian Commodity Exchange and the Ministry of Trade and Regional Integration held a discussion on the Draft Law on the Registration and Protection of Geographical Indications in Bishoftu City March 19/ 2024.

Tadese Worku, Lead executive of Traditional knowledge, said that one of the main tasks of the Ethiopian Geographical Indications System Project, which is being implemented with the support of the French government, is to prepare a law that will govern the sector. He also explained that the workshop was prepared to gather imputes by criticizing the bill by experts.

The Deputy Director General of the Ethiopian Intellectual Property Authority, Edalu Mosisa, stated that under the home economic reform plan to properly utilize its natural and man-made resources for economic growth. GI then help to protect our well known agricultural & community knowledge and benefit the community

In the discussion, ideas were presented and discussed on the basic contents of the draft declaration, definitions, registration process, the authority’s responsibility, the role of other actors and other issues.

በመልክዓ ምድራዊ አመልካቾች ምዝገባና ጥበቃ ረቂቅ ህግ ላይ ውይይት ተካሄደ

=== === === === ===

በመልክዓ ምድራዊ አመልካቾች ምዝገባና ጥበቃ ረቂቅ ህግ ላይ ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር፣ ጅማ ዩኒቨርስቲ፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለሙያዎች በቢሾፍቱ ከተማ መጋቢት 10/2016 ውይይት አካሄዱ፡፡

የማበረሰብ ዕውቀት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ታደሰ ወርቁ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየተተገበረ ባለው የኢትዮጵያ የመልክዓ ምድራዊ አመልካቾች ምዝገባና ጥበቃ ሥርዓት ፕሮጀክት ሥራ ዘርፉን የሚመራ ህግ ማዘጋጀት አንዱና ዋነኛ ተግባር መሆኑን አውስተው ረቂቅ የህግ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለባለሙያዎች ውይይት መቅረቡን ተናግረዋል፡፡ መድረኩም ረቂቅ አዋጁን በባለሙያዎች በማስተቸት ግብዓቶችን ለመሰብሰብ የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ም/ል ዋና ዳይሬክተር እዳሉ ሞሲሳ ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሃብቶችን ለኢኮኖሚዊ ዕድገት በአግባቡ ለመጠቀም በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅድ ላይ መቀመጡን ገልጸው ያሉንን ታዋቂ የግብርናና ሌሎች ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ዕውቀቶችና ውጤቶችን በመልክዓ ምድራዊ አመልካች ሥርዓት ማስጠበቅ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በረቂቅ አወጁ መሰረታዊ ይዘቶች፣ ትርጓሜዎች፣ የምዝገባ ሂደት፣ የባስልጣኑ ኃላፊነት፣ የሌሎች ተዋናዮች ሚና እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

——-

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS