ፓናል ውይይት ተካሄደ

ፓናል ውይይት ተካሄደ

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ባከበረው የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን ላይ ወጣት ኢንተርፕርነርሺፕ፣ ኢኖቬሽን እና የስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የአእምሯዊ ንብረት ትመናና ፋይናንሲንግን በማስመልከት ሁለት አውደ ጥናቶች በአዲስ አበባ ሚያዝያ 20/2014 ዓ.ም አካሄደ፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ ከከፍተኛ ትምህርትና ምርምርና ስርጸት ተቋማት፣ ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከባለድርሻ አካላት፣  ተወካዮች ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

ጠበቃ፣ የህግ አማካሪና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ቶማስ ገብረሚካኤል የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ለወጣቶች የፈጠራ እና የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት በማስመልከት አውደ ጥናት አቅርበዋል፡፡ የወጣቱን አጠቃላይ ነባራዊ ገፅታ፣ የወጣቱ የሥራ አጥነት ገፅታና አበይት ተግዳሮቶች ፣ወጣቱ እና የሥረ ፈጠራ ባህል ነባራዊ ሁኔታ በተለይም የሥራ አጥነት አጀንዳ እና የሥራ ፈጠራ አጀንዳ ተወራራሽነት እና ተቃርኖ ፣የወጣቱን ጉዳይ ጥገኛ የተጠቃሚነት አጀንዳ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ እና የማህበራዊ ፖሊሲ ጉዳይ ብቻ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ የወጣቱን የሥራ ፈጠራ (ግኝት) ኃይል ለአጠቃላዩ ሃገራዊ እድገት ጉልህ ሚና እንዳይጫወት ያለው ተፅዕኖን በተመለከተ ንድፈ ሃሳባዊ ትንታኔ አቅርበዋል፡፡

የወጣቱ የሥራ ፈጠራ አቅም ለአጠቃላይ ሃገራዊ እድገት ጉልህ ሚና ሊጫወት ይገባል ከተባለ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ (የግሉ ሴክተር እና የልማት ድርጅቶች) ተቋማት ከፖሊሲ ማዕቀፍ እስከ አተገባበር የጋራ የተቀናጀ አጀንዳ እና አሰራር ሊያዳብሩ እንደሚገባም አቶ ቶማስ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

በትዕግስት ደሱ (ፒኤችዲ) የቀረበው የአውደ ጥናት ጽሁፍ የአእምሯዊ ንብረት ትመናና ፋይናንሲንግ ሲሆን ሃሳብ በማመንጨት የፈጠራ ስራ ለሰሩ ባለመብቶች የአእምሯዊ ንብረት እሴቶቻቸውን በመተመንና እንደ ማስያዥያ በመጠቀም ብድር ማግኘት የሚያስችላቸውን የፖሊሲና የአሰራር መገምገም ላይ ያጠነጠነ እንደነበር ተብራርቷል፡፡ በአእምሯዊ ንብረት የተደገፈ የንግድ ስራ ትርፋማነትን ለማሳደግ፣ ውጤታማ ለመሆንና ከተፎካካሪ ተሸሎ ለመገኘት ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ በቀረበው ጽሁፍ ተገልጿል፡፡

መድረኩን በአወያይነት የመሩት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ፒኤችዲ) በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በምትመራበት የዕውቀት መር ኢኮኖሚ ውስጥ በዜጎች በተለይም በወጣቶች የዕለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ አእምሯዊ ንብረት የሚኖረውን አበርክቶ በመገንዘብ ወጣቶች በፈጠራው ዘርፍ እንዲሳተፉ ማበረታታት፣ ማንቃትና መደገፍ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS