የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን አከባበር የፈጠራ ስራዎች ዓውደ-ርዕይ መርሃ-ግብር
የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን አከባበር ሚያዝያ 19/2015 በተካሄደው የፈጠራ ስራዎች ዓውደ-ርዕይ የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ተጠናቀቀ፡፡
ለሁለት ቀናት በሳይንስ ሙዚየም ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ሲካሄድ በቆየው ዓውደ-ርዕይ ከ50 በላይ የፈጠራ ሥራዎች በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግ፣ በሽመና፣ በሶፍት ዌር፣ በእጅ ሥራ፣ በሥነ-ጽሁፍ፣ በሥነ-ጥበብ፣ በባህል መድሃኒትና ሌሎችም ዘርፎች የፈጠራ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ሽልማትና የዕውቅና ሰርተፊኬት ለአቅራቢዎች ተበርክቷል፡፡
የባለስልጣኑ ም/ል ዋና ዳ/ር እንዳሉ ሞሲሳ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የሴቶች ማብቃት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወይንሸት ገለሶ ሽልማትና የዕውቅና ሰርተፊኬቱን ሲሰጡ የፈጠራ ባሙያዎቹን በማበረታታት ከዚህ በላይ የተሻሉ የቴክኖጂ ውጤቶችን እንዲያመነጩ የዘርፉ ተቋማትና የግሉ ዘርፉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡