World IP Day-2023

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን በድምቀት ተከበረ

World IP Day colorfully celebrated

*** *** *** *** *** *** *** ***

“አእምሯዊ ንብረትና ሴቶች፡ ኢኖቬሽንና ፈጠራን ማፋጠን” የሚል መሪ ሃሳብ ያነገበው የዘንድሮ የአለም አእምሯዊ ንብረት ቀን ክቡራን ሚኒስትሮች የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ ባለድርሻና ተባባሪ ተቋማት፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ተቋማት፣ የፈጠራ ባለመብቶች፣ የማህበራትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ሚያዝያ 18 እና 19፣ 2015 ዓ.ም ተከበረ፡፡

በዝግጅቱ የመክፈቻ መርሃ-ግብር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኢታ ሁሪያ አሊ፣ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል፡፡

ሴቶች ፈጠራን በማመንጨት፣ አእምሯዊ ንብረትን ጥቅም ላይ በማዋል፣ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የማህበረሰቡን ችግር በመፍታትና ሌሎችንም ፋይዳዎች በማበርከት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑና አለም አሁን ለደረሰችበት የቴክኖሎጂ እድገት የሴቶች አሻራ በጉልህ የሚጠቀስ መሆኑ ክቡራን ሚኒስትሮቹ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆየውንና ከ50 በላይ የፈጠራ ሥራዎች የቀረቡበትን የዝግጅቱ የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ ክቡራን ሚኒስትሮቹ የከፈቱ ሲሆን በዝግጅቱ የተገኙ ተሳታፊዎችና ሌሎችም ጎብኚዎች ጎብኝተዋል፡፡      

የፈጠራ ስራዎችን በማስመዝገብ ደረጃ ሴቶች ያላቸውን ተሳትፎ የተመለከተ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮና የሃገራችን ልምድ በባለስልጣኑ የንግድ ምልክት ሥራ አስፈጻሚ ትዕግስት ቦጋለ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ የሚያጠነጥን ተቋም ተኮር የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስራና ክሎት ሚኒስቴር፣ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም፣ የንግድ ምልክት ኤጀንት እንዲሁም የባለስልጣኑ ተወካዮች ሃሳቦችን አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

World IP Day, 2023 having a theme “women and IP: accelerating innovation and creativity” colorfully celebrated with the presence of higher officials, representatives of government and private institutions, IP right holders and media at Science Museum on April, 2023.

At the opening ceremony, Her excellency Dr. Ergoge Tesfaye, Minister to Ministry of women and social affairs, Her excellency Huria Ali, State Ministry to Innovation and Technology and His excellency Dr. Ermias Yemanebirhan, former Director General of Ethiopian Intellectual Property Authority addressed opening remarks.

The celebration consist exhibition of creative works that lasts for two days and a panel discussion focusing on the theme and media engagement. Ministry of women and social affairs, Development Bank of Ethiopia and National ID Program collaborated with Ethiopian Intellectual Property Authority to commemorate this International Day of IP

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS