የከተማ መስተዳድሮችና የክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ለማጠናከር ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከከተማ መስተዳድሮችና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎችና ኤጀንሲዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ግንቦት 16/2014 ዓ.ም በአዳማ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ፒኤችዲ) የበለጸጉ አገራት የእድገታቸው ሚስጥር ለፈጠራ፣ ለኢኖቬሽንና  ለአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ትኩረት በመስጠታቸው እንደሆነ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡ በሀገራችንም የአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ የዕድገት አንቀሳቃሽ መሳሪያ በማድረግ የፈጠራ ባለመብቶች ስራዎቻቸውን እንዲያስጠብቁ፣ እንዲያለሙና የገበያ ትስስር በመፍጠር ባለመብቱን፣ ማህበረሰቡንና ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ በህዝቡ ዘንድ ማሳደግ፣ በየተቋማቸው የሚገኙትን ባለሙያዎች ማሰልጠን፤ የአእምሯዊ ንብረት አደረጃጀቶቻቸውን በመፈተሸ የአእምሯዊ ንብረት ስርዓት መዘርጋት፤ የዘርፉን ህጋዊ ተፈጻሚነትና የማመልከቻ ቅበላና የምርመራ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት ስልጠናው ጉሉህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የካውንስሎችና ክልሎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኑርልኝ ኮኩ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ስራንና ሀብትን ለመፍጠር የምትመች ሀገር መገንባት ርዕይ ሰንቆ በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና በድጅታላይዜሽን የትኩረት መስኮች በመስራት ላይ እንደሚገኝ በአቀረቡት የመወያያ ጽሁፍ አብራርተዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ጽንስ ሃሳብ፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አደረጃጀት፣ ኃላፊነት፣ ተግባር እና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች/ኤጀንሲዎች ጋር በቅንጅት በመሰራት ላይ በሚገኙ ጉዳዮች ዙሪያ የክልል ቅ/ጽ/ቤቶች አስተባባሪ ተድላ ማሞ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች የመብት አስተዳደር፣ የምዝገባ መስፈርቶች፣ የምዝገባ ሂደቶችን በማስመልከት የመወያያጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

በቀጣይ ቀን በሚኖረው መርሃ ግብር የንግድ ምልክትና  የቅጅ መብት ምንነት፣ የህግ ማዕቀፎች እና የምዝገባ ስርዓቶች በማስመልከት የመወያያ ጽሁፎች *ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው እንደሆነ የስልጠናው አስተባባሪ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከከተማ መስተዳድሮችና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎችና ኤጀንሲዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ግንቦት 16/2014 ዓ.ም በአዳማ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ፒኤችዲ) የበለጸጉ አገራት የእድገታቸው ሚስጥር ለፈጠራ፣ ለኢኖቬሽንና  ለአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ልማት ትኩረት በመስጠታቸው እንደሆነ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን የአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ የዕድገት አንቀሳቃሽ መሳሪያ በማድረግ የፈጠራ ባለመብቶች ስራዎቻቸውን እንዲያስጠብቁ፣ እንዲያለሙና የገበያ ትስስር በመፍጠር ባለመብቱን፣ ማህበረሰቡንና ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ በህዝቡ ዘንድ ማሳደግ፣ በየተቋማቸው የሚገኙትን ባለሙያዎች ማሰልጠን፤ የአእምሯዊ ንብረት አደረጃጀቶቻቸውን በመፈተሸ የአእምሯዊ ንብረት ስርዓት መዘርጋት፤ የዘርፉን ህጋዊ ተፈጻሚነትና የማመልከቻ ቅበላና የምርመራ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት ስልጠናው ጉሉህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የካውንስሎችና ክልሎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኑርልኝ ኮኩ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ስራንና ሀብትን ለመፍጠር የምትመች ሀገር መገንባት ርዕይ ሰንቆ በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና በድጅታላይዜሽን የትኩረት መስኮች በመስራት ላይ እንደሚገኝ በአቀረቡት የመወያያ ጽሁፍ አብራርተዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ጽንስ ሃሳብ፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አደረጃጀት፣ ኃላፊነት፣ ተግባር እና ከክልሎች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች/ኤጀንሲዎች ጋር በቅንጅት በመሰራት ላይ በሚገኙ ጉዳዮች ዙሪያ የክልል ቅ/ጽ/ቤቶች አስተባባሪ ተድላ ማሞ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች የመብት አስተዳደር ፣ የምዝገባ መስፈርቶች፣ የምዝገባ ሂደቶችን በማስመልከት የመወያያጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

በቀጣይ ቀን በሚኖረው መርሃ ግብር የንግድ ምልክትና  የቅጅ መብት ምንነት፣ የህግ ማዕቀፎች እና የምዝገባ ስርዓቶች በማስመልከት የመወያያ ጽሁፎች *ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው እንደሆነ የስልጠናው አስተባባሪ ገልጸዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS