የኢትዮጵያ የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ በይፋ ተከፈተ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን #EIPA ከዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት #WIPO ባገኘው ድጋፍ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤን ለማሳደግ የላቀ ድርሻ የሚኖረውን የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ ዛሬ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም በይፋ ከፈተ፡፡

አእምሯዊ ንብረት ቀጣይነት ያለው እና ሰፊ ልማትን በማበረታታት ፈጠራን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስተዋወቅ ወሳኝ መሆኑን ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ሀገሮች በተቋማት የሚመሩ ስትራቴጂካዊ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ ፕሮግራሞች ሲኖራቸው ብቻ እንደሆነ መርሃ-ግብሩን በከፈቱበት ወቅት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ፒኤችዲ) ተናግረዋል፡፡ የሀገራዊ የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ ምስረታ በብዙ ደረጃዎች እና በባህሪው አእምሯዊ ንብረትን የልማት መሳሪያ ለማድረግ ለሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ወሳኝ መሆኑን እንዲሁም የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ መመስረት የማንኛውም ሀገር የእድገት ደረጃ እና የፈጠራ አቅምን የሚያሳድግ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

ይህን የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ ለማቋቋም ከተከናወኑ ተግባራት ዋና ዋናዎቹ የቢዝነስ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ሰልጣኞች መመልመል፣ የትምህርት ስርዓት መቅረጽ እና የማሰልጠኛ ሞጅሎች ሃገራዊ የማድረግና የመተርጎም ስራዎች እንደሚገኙበት ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

በአሰልጣኞች ስልጠናው ላይ ከከፍተኛ ትምህርት፣ ከምርምርና ስርጸት ተቋማት፣ ከጋራ አስተዳደር ማህበራት፣ ከፈጠራ ባለሙያዎች እና ከአእምሯዊ ንብረት ወኪሎች የተወጣጡ ሰልጣኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS