የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርምያስ የማነብርሀን ከ59ኛዉ የዓለም አቀፍ አዕምሯዊ ንብረት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የአእምሯዊ ንብረት ድርጅት አካዳሚ (WIPO Academy) ዳይሬክተር ሚ/ር ሸሪፍ ሳዳላህ ጋር ተወያዩ። በውይይቱ የአእምሯዊ ንብረት አካዳሚ በኢትዮጵያ ለማቋቋም የተጀመረውን ስራ በማጠናቀቅ በመጪው የፈረንጆች አመት የካቲት ላይ ስራ ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ወጣቶችና ተዳጊዎች ላይ ያተኮረ የአቅም ማሳደግያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ለመጀመር የተስማሙ ሲሆን ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሁለተኛ ድግሪ ትምህርትና የመካከለኛ ግዜ ስልጣን በመጪው የፈረንጆች አዲስ አመት እንደሚመቻች ሚ/ር ሸሪፍ ለአቶ ኤርምያስ ገልጸውላቸዋል። አቶ ኤርምያስ በበኩላቸው አካዳሚው ለጽ/ቤቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።