የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲ የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት ጋር በመተባበር ብሔራዊ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲ ለማዘጋጀት የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ውጤት ላይ ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር ሚያዝያ 03/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ምክክር አካሄደ፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ፒኤችዲ) ባለስልጣኑ በመተግበር ላይ በሚገኘው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ ብሔራዊ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲ በመቅረጽ ተግባራዊ ማድረግ ትኩረት የተሰጠው ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በሃገራችን የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተደረጉ አዳዲስ የፖሊሲ፣ የህግና የአሰራር ማሻሻያዎች በመኖራቸው በጅምር ላይ የነበረውን ፖሊሲ እነዚህን ለውጦች እና በዘርፉ ያሉ እድገቶችን ያማከለ እንዲሆን ፖሊሲውን እንደገና ማዘጋጀት እንዳስፈለገ አክለው ገልጸዋል፡፡

ሃገራዊ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲን እንደገና ለማዘጋጀት የተለያዩ ከዘርፉ ጋር ተያያዠነት ያላቸው ሰነዶችን በመመርመር፣ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመወያየትና በተለያዩ ሴክተሮች ከሚገኙ ሃገራዊ ፖሊሲዎች ጋር የተጣጣመ ለማድረግ በሚያስችል አግባብ የፍላጎት የዳሰሳ ጥናቱ መደረጉን በመድረኩ ላይ ተገል ተገልጿል፡፡

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት አማካሪ ጌታቸው መንግስቴ ብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲ ለመቅረጽ አስፈላጊ የሆነውን የፖሊሲ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ውጤት አቅርበዋል፡፡ የጥናቱ ውጤትም 13 ቁልፍ የፖሊሲ ጭብጦች የተለዩ እንደሆነ አቶ ጌታቸው አብራርተዋል፡፡

በቀረበው የዳሰሳ ጥናት መሰረት በተደረገው የባለድርሻ አካላት ውይይት መግባባት ላይ የሚደረስባቸውን የፖሊሲ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ ሃገራዊ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲና የማስፈጸሚያ ስልቶች የሚነደፉ እንደሆነ በመድረኩ ተብራርቷል፡፡ የቀረበው የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ተቀባይነት በማግኘቱ የውይይቱ ተሳታፊዎች የሰጡትን ገንቢ የፖሊሲ ማዳበሪያ ግብዓቶችን በማካተት የፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻ ተግባር እንደሚጀመር ከመድረኩ ተብራርቷል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS