የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃን ለማጠናከር የክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲዎች/ቢሮዎች ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ተጠቀሰ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከጋምቤላ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በአእምሯዊ ንብረት ምንነትና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አደረጃጀት እንዲሁም ኤጀንሲው የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ማመልከቻ ቅበላና የፎርማሊቲ ምርመራ ተግባራትን ማከናወን እንዲጀምር የሚያስችል የውይይት መድረክ ጥር 5/2014 ዓ.ም በጋምቤላ አካሄዱ፡፡

­­­የክልሉ ም/ር/መስተዳድር እንዲሁም የክልሉ የሳ/ቴ/ኤጀንሲ ኃላፊ ያሲን በላይ ያሲን የውይይት መድረኩን ዓላማ እና ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ በመከናወን ላይ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጻ አድርገዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ ተድላ ማሞ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃን በክልሎች ተደራሽ ለማድረግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ከመክፈት ባለፈ ከክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ/ቢሮዎች ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የጋምቤላ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በክልሉ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች የምዝገባ አገልግሎት መስጠት  እንዲጀምር የድጋፍና የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረክ እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃን ለማጠናከርና በክልሎች ተደራሽ ለማድረግ የክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲዎች/ቢሮዎች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ በበጀት ዓመቱ የክልሉን ሳ/ቴ/ኤጀንሲ የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ትሪቡናል ዳይሬክተር አብርዱ ብርሃኑ የክልሉ የሳ/ቴ/ኤጀንሲ በክልሉ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች ጥበቃ እንዲያገኙ የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ማመልከቻ ቅበላና የፎርማሊቲ ምርመራ ተግባራትን በማከናወን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባው በጽሁፋቸው አመላክተዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለኤጀንሲው በሚሰጠው ተከታታይ ድጋፍ በክልሉ ዘርፉን የተመለከቱ የምክርና መሰል የሙያ ድጋፍ የሚያደርግበትን አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS