የአእምሯዊ ንብረት መብቶች በፋይናንስ አቅርቦት ምንጭነት መጠቀም እንደሚቻል ገለጻ ተደረገ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው መድረክ ላይ በመገኘት ስለ አእምሯዊ ንብረት መብቶች ምንነት፣ አእምሯዊ ንብረትና ኢኖቬሽን ያላቸው ግንኙነት እንዲሁም አእምሯዊ ንብረትን እንደ ፋይናንስ ምንጭነት መጠቀም የሚቻልበትን አሰራር በተመለከተ ጥር 19/2014 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ገለጻ ተደረገ፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ፍሬው ተገኝ በብሄራዊ ባንክ ወደ ስራ የገባውን አዋጅ ቁጥር 1147/2012 ፣አዋጁን ማስፈጸሚያ መመሪያዎች ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን ይህም ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዞ መበደር የሚያስችል የህግ ማእቀፍ እንደሆነ፤ በዚህ አዋጅ ተንቀሳቃሽ ንብረት ተብለው ከተመደቡት መካከል የአእምሯዊ ንብረት አንዱ ሲሆን የአእምሯዊ ንብረቶችን ምዘና፣ትመና እና የአእምሯዊ ንብረት መብቶች በፋይናንስ አቅርቦት ምንጭነት መጠቀም እንደሚቻል ገልጻ አድርገዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS