የባለስልጣኑ የ2014 ዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ እንደሆነ ተጠቆመ

የባለስልጣኑ የ2014 ዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ እንደሆነ ተጠቆመ

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በዝግጅት፤ በቁልፍ ተግባራት እና በአበይት ተግባራት ዋና ዋና የአፈፃፀም ምዕራፎች የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሰኔ 03/2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ አካሄደ፡፡

ባለስልጣኑ በ2014 በጀት ዓመት የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ጥበቃ ማጠናከር፣ የአእምሯዊ ንብረት ልማት ማሳደግ፣ የህግ ተፈጻሚነትና ቅንጅታዊ አሰራር ማሳደግ፣ የአእምሯዊ ንብረት ትምህርትና ስልጠና ማጎልበት፣ ውጤታማ ተቋም መገንባት በሚሉ አምስት የትኩረት መስኮች ዕቅድ ታቅዶ ሲተገበር እንደቆየ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ወንድወሰን ግዛቸው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 4881 የአእምሯዊ ንብረት ማመልከቻዎችን ለመቀበል ታቅዶ 3961 ማመልከቻዎችን መቀበል የተቻለ ሲሆን ከቀረቡት ማመልከቻዎች መካከል ለ3820 የአእምሯዊ ንብረት ባለመብቶች የባለቤትነት መብት መሰጠቱ በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል፡፡  

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰጠው የአእምሯዊ ንብረት መብቶች የምዝገባ አገልግሎቶች 22,090,409 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 21,883,411 ብር የእቅዱን 99.1 መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመባቸው አራት ዓላማዎች መካከል የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ በህዝቡ ዘንድ ማሳደግ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን የአእምሯዊ ንብረት ጽንስ ሃሳብ፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ አስፈላጊነት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ 28 ስልጠናዎች በዋና ዋና የክልል ከተሞችና ከተማ መስተዳድሮች ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የፈጠራ ባለመብቶች፣ የምርምርና ስርጸት ተቋማትና የንግድ ማህበረሰብ መሰጠቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ጥበቃ እንዲያገኙና እንዲለሙ ለማድረግ ከተከናወኑ የአሰራር ስርዓት መካከል የማህበረሰብ እውቀት ረቂቅ ህግ፣ የመልካምድራዊ ምንጭ አመላካች፣ የባለስልጣኑ ማሻሻያ አዋጅ፣ እንዲሁም የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲ ረቂቅ የህግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው የባለድርሻ አካላት ውይይት መደረጉና ገንቢ ግብዓቶች እንደተሰበሰበ ተገልጿል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የቀረበውን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተደርጓል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) የውይይት መድረኩን በመሩበት ወቅት በበጀት ዓመቱ የተገኘውን ውጤት በማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ ለቀጣይ በጀት ዓመት ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የአእምሯዊ ንብረት ባለመብቶች ስራዎቻቸውን ባሉበት ማመልከቻ ማቅረብ እንዲችሉ ለማድረግ በንግድ ምልክት ዳይሬክቶሬት በመሰጠት ላይ የሚገኘውን አገልግሎት ማጠናከር እንዲሁም በፓተንት ዘርፍ አገልግሎቱን ለመስጠት የተጀመረውን የዝግጅት ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር እንዳሉ ሞሲሳ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች እንደሆኑ ጠቁመው አዳዲስና የማሻሻያ የህግ ማዕቀፍ ስራዎች ማጠናቀቅ፣ የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ፣ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራዎችን ማጠናከር እና የሚዲያ ግንኙነትን ማሻሻል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS