በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም በእስያ የሚገኙ በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮችን የሚያግዘው የፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኩባንያ አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስን በመጠቀም በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ በእስያ የሚገኙ አርሶ አደሮችን የሚያግዘው የፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኩባንያ

ትርጉም፡ ዮሐንስ አፈወርቅ
አርትኦት ፡ ብሩክ ወርቅነህ

ሪከልት በእስያ የሚገኙ በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮችን ዘርፈ ብዙ አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን መሰረት በማድረግ ለመደገፍ የቀረበ መፍትሄ ሲሆን፤ በተለይም በዲጂታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂን እንደ መፍትሄ በመጠቀም ነው፡፡ ስልተ ቀመሮቹን (አልጎሪዝሞቹን) በአእምሯዊ ንብረት ስርዓት ማስጠበቁ ለኩባንያው ያለው ጠቀሜታ ተረጋግጧል፡፡


(PHOTO: RICULT)

ኡሰማን ጃቪድ የዓለም አቀፉ ሪከልት ኩባንያ እንዲሁም የፓኪስታኑ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሲሆን ምህንድስናን በፓኪስታን ካጠና በኋላ ኔስትል የተባለውን ድርጅት ከመቀላቀሉ በፊት ኤግዞን ለተሰኘው ድርጅት የማዳበሪያ የሽያጭ ሰራተኛ ነበር፡፡ ታዲያ በዚህ ቦታ በመስራት ላይ ሳለ ሰፊ ድርሻ ላለው ስማርት ባልሆኑ የሞባይል ስልኮች አማካይነት የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት አቅራቢ አባል የነበረው፡፡ ከስራውም ባገኘውም ልምድ እንዴት ቀላል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማገልገል እንደሚቻል ተረዳ፡፡ በግብርናው ዘርፍ ላይ መሰማራቱም በአነስተኛ ማሳ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በሚገባ እንዲገነዘብ አድርጎታል።


የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ህብረት ፊንቴክን በግብርናው ማስተዋወቅ

እ.ኤ.አ. በ 2014 ኡስማን በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች የሚያቃልልበትን መንገድ ለመፈለግ በማሰብ በገዛ ፈቃዱ ከሥራው በመልቀቅ የቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ድግሪውን በፈጠራና ዓለምአቀፍ ቢዝነስ ለመከታተል የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ኤምአይቲ)ን ተቀላቀለ፡፡ በዚያም ቤተሰቦቹ በእርሻ ስራ ይተዳደሩ ከነበሩትና ከኡስማን ጋር ተመሳሳይ ዓላማ አንግቦ ከታይላንድ ከመጣው ከአክሪት አናሌካ ጋር ተዋወቀ፡፡ በኋላም የዚሁ ተቋም ተማሪዎች የሆኑት ገብርኤል ቶሬስና ጆናታን ስቶለር ቡድኑን ተቀላቀሉ፡፡

በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ ገበሬዎችን ለመርዳት የቀረጹት የመረጃ ትንተናን በመጠቀም ለግብርናው የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በተቋሙ የፈጠራ ስራዎችን ለመደገፍ በሚሰራው ኤም.አይ.ቲ አክስለሬተር ፕሮግራም (MIT Accelerator Program) ተቀባይነት በማግኘቱ ለመነሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ አስቻላቸው፡፡ ፕሮጀክቱ የእስያ ባለሀብቶችን ጭምር ቀልብ በመሳቡ ሲጠናቀቅ ኡስማንና ጓደኞቹ ከተቋማዊ ባለሃብቶች ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡

“Ricult“ የሚለው የካምፓኒው ስያሜም ከእንግሊዝኛው “Agriculture” ከሚለው ቃል ውስጥ የመሀለኞቹን ፊደላት ብቻ በመውሰድ የተገኘ ነው (Ag-“ricult”-ure) ፡፡ ከላይ በተጠቀሱት አራት የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የተቋቋመው ካምፓኒም ዋና መቀመጫውን በቦስተን አድርጎ እ.ኤ.አ በ2015 ተመሰረተ፡፡ ቀጥሎም በፓኪስታን እንዲሁም በአክሪት የሚመራው ሌላኛውን ቅርንጫፍ በታይላንድ ከፍቷል፡፡ ጆናታን ዋና የቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ እንዲሁም ገብርኤል ዋናው የስትራቴጂ ባለሙያዎች ሲሆኑ ሪከልት እ.ኤ.አ በጥር2022 አገልግሎቱን በቬትናም መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፊንቴክ ሶሉሽን የገበሬዎችን የካፒታል ተደራሽነት ያመቻቻል

እንደ ኡስማን እይታ ከሆነ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ካሉባቸው ችግሮች አንዱና ዋነኛው የካፒታል ተደራሽነት ነው፡፡ መደበኛ የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባለመሆኑ በአነስተኛ ማሳ ለሚተዳደሩ አርሶ አደሮች በተመጣጣኝ ወለድ ወይም ክፍያ  መነሻ ገንዘብ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል፡፡ ይህም ገበሬዎቹን ህገወጥ አራጣ አበዳሪዎችጋ  እንዲሄዱና በዚህም ምክንያት ከማይወጡት የድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲዘፈቁ ያደርጋቸዋል፡፡ኡስማን እንዳለው ‹‹ በተደጋጋሚ ይበደራሉ እዳቸውን መልሰው መክፈል ግን አይችሉም››፡፡


እንደ ኡስማን እይታ ከሆነ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ካሉባቸው ችግሮች አንዱና ዋነኛው የካፒታል ተደራሽነት ነው፡፡ መደበኛ የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባለመሆኑ በአነስተኛ ማሳ ለሚተዳደሩ አርሶ አደሮች በተመጣጣኝ ወለድ ወይም ክፍያ መነሻ ገንዘብ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል፡፡ ይህም ገበሬዎቹን ህገወጥ አራጣ አበዳሪዎችጋ እንዲሄዱና በዚህም ምክንያት ከማይወጡት የድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲዘፈቁ ያደርጋቸዋል፡፡ኡስማን እንዳለው ‹‹ በተደጋጋሚ ይበደራሉ እዳቸውን መልሰው መክፈል ግን አይችሉም››፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው መደበኛ የሆነ የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባለመሆኑ ምክንያት አርሶ አደሮቹ የእርሻ ግብዓቶችን በብድር ወደ ሚያቀርቡላቸው ደላሎች ይሄዳሉ፡፡ ግብአቶቹም ጥራታቸውን ያልጠበቁና ከመደበኛው የገበያ ዋጋ ከፍ ባለ ዋጋ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ሰብሉ በሚሰበሰብበትም ወቅት ደላሎቹ ሰብሉን ለመግዛት የመጀመሪያዎቹ ባለመብቶች ይሆናሉ፡፡ በዚህ መልኩ አርሶ አደሮቹ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባሉ፡ሲል ኡስማን ይገልጻል፡፡

የመረጃ ትንተና ለመደበኛ የባንክ ስርዓት በር ይከፍታል

አንድ አርሶ አደር ከሪከልት ጋር የሚሰራ ከሆነ ካምፓኒው ብድር ከሚያቀርብለት ባንክ ጋር ያገናኘዋል፡፡ የባንኩ እምነት የሚመሰረተውም በመረጃ ትንተናውና የሪከልት የብድር ታሪክ ላይ መሆኑንም ኡስማን ያስረዳል፡፡

ከዚያም ሪከልት ከግብዓት አቅራቢ ካምፓኒዎች ጋር በመነጋገር አርሶ አደሮቹ ጥራቱን የጠበቀ ግብዓት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ካምፓኒው የአርሶ አደሮቹን ሰብል ከተዘራበት ጊዜ አንስቶ እስከሚሰበሰብበት ወቅት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እያንዳንዱን ሂደት ላይ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ሰብሉን በቦታው መገኘት ሳይኖርባቸው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ክትትል በማድረግና ለአርሶ አደሮቹም እንዴት የተሻለ ምርታማነት ሊኖራቸው እንደሚችል ምክረ ሃሳብ በማቅረብ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡ ሰብሉ በሚደርስበት ወቅትም ሪከልት ያለምንም ደላሎች ጣልቃ ገብነት ምርቱ በቀጥታ ለፋብሪካዎች የሚቀርብበት ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

ኡስማን እንደገለጸው የድርጅቱ ራዕይ “ሪከልትን ለአርሶ አደሮች ተመራጭ የዲጂታል ፋይናንሺያል መፍትሄ ማድረግ ሲሆን፤ ባንኮች ለአርሶ አደሮች ለማበደር የማይፈልጉባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶችም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለማጥራት እየሰራ እንገኛለን ፡፡ ባንኮቹ የኛን መፍትሄ እንዲጠቀሙ ከረዳናቸው የባንክ ተጠቃሚ ላልሆኑት ወይም ከባንክ ስርአት ውጪ ለሆኑት አርሶ አደሮች መደበኛ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አማራጭ መሆን ይችላል፡፡”


በአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ የጎለበቱ መተግበሪያዎች ለገበሬዎች

ኡስማን ሪከልትን እንደ አንድ የመረጃ ትንተና ድርጅት ነው፡፡ መረጃን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለምሳሌ ከአርሶ አደሮች፣ ከርቀት ዳሰሳ ወይም በእንግሊዝኛው ሪሞት ሴንሲንግ፣ ከአጋር ተቋማትና ከግብዓት አቅራቢ ድርጅቶች ፤እነዚህን የተሰበሰቡ መረጃዎች በስልተቀመሮች በማደራጀት በቋሚነት መተግበሪያዎቹን ለማሻሻል ይጠቀምበታል፡፡

ሪከልት X ሰሌዳ – የመረጃ ትንተና አጠቃቀም በግብርና

ሪከልት X ሰሌዳ የሪከልት ዋና መተግበሪያ ሲሆን ድርጅቱ አጠቃላይ የመረጃ ትንተናውን ለባንኮችና በእርሻ ቢዝነስ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች የሚያሳይበትና የሚያቀርብበት መተግበሪያ ነው፡፡ መተግበሪያው ማሽኖችን በማስተማርና ሰው ሰራሽ የመረዳት ችሎታ ወይም በእንግሊዝኛው ማሽን ለርኒንግና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ መሰረቱን ያደረገ ወቅታዊ ትንታኔን ያካተተ ሲሆን ይህም ትንበያንና ምርመራን ለማድረግ ይረዳል ሲል ኡስማን ይገልጻል፡፡

ሪከልት ፋርመር መተግበሪያ – ሰፊ መረጃን በግብርና ላይ መጠቀም

ሌላኛው የሪከልት መተግበሪያ “Farmer app” ሲሆን ይህም በሞባይል አማካኝነት ለአርሶ አደሮች ምርታማነታቸውንና ትርፋማነታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚረዳቸው መረጃ የሚቀርብበት ነው፡፡ ሪከልት ከዚህ በተጨማሪ “Field agent app” የተሰኘ መተግበሪያም ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን ይህም የተለያዩ ተቋማት ለምሳሌ የባንክ፣ የፋብሪካዎችና የመሳሰሉት ተቋማት ባለሙያዎች/ወኪሎች በአካባቢያቸው መረጃ ለመሰብሰብ እና ለመጠቀም የሚያስችላቸው መተግበሪያ ነው፡፡

እንደ ኡስማን ገለጻ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ወደ 300,000 የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከታይላንድ እንዲሁም 200,000 የሚሆኑት ደግሞ ከፓኪስታን “Farmer app” የተሰኘውን መተግበሪያ ይጠቀማሉ፡፡ የኛ ትልቁ ግባችን ማንኛውም የስማርት ስልክ ያለው አርሶ አደር መተግበሪያውን እንዲጠቀም ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2022 ሪከልት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ሊኖሩት እንደሚችል ኡስማን ተስፋ ያደርጋል፡፡

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠበቅ የአዕምሯዊ ንብረት አስፈላጊነት

ሪከልት ቁልፍ የሆኑ አልጎሪዝሞቹን/ስልተ-ቀመሮቹን፣ስሙንና አርማውን በአዕምሯዊ ንብረት ያስጠበቀ ሲሆን ጥበቃውም ተፈጻሚነቱ በዩናይትድ ስቴትስ ነው፡፡ ኡስማን የአዕምሯዊ ንብረትን የጎላ ሚና ሲያሰምርበት ‹‹ቴክኖሎጂዎችን በአዕምሯዊ ንብረት ማስጠበቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ባለሀብቶች ከጀማሪ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ሊያመነቱ ይችላሉና››፡፡

በግብርናው ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ከሪከልት ጋር መቅረፍ

‹‹በእኛ እምነት ትልቁ መፈታት ያለበት ችግር የአርሶ አደሮቹ የፋይናንስ ተደራሽነት ሲሆን ይህ ጉዳይ በአግባቡ ካልተቃኘ ሌሎች በግብርናው ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አዳጋች ያደርገዋል፡፡››

ይላል ኡስማን አክሎም ‹‹ይህንን የሚያቀላጥፉ ሌሎች መተግበሪያዎችን መገንባታችንን መቀጠልና በሌሎች የእስያ ሀገራትም ቅርንጫፎች መክፈት እንፈልጋለን›› ብሏል፡፡

የሪከልት መተግበሪያዎች ተደራሽነት የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ለሆኑ አርሶ አደሮች ብቻ ሲሆን እንደ ኡስማን ገለጻ በታይላንድ 50 በመቶ የሚሆኑት አርሶ አደሮች የስማርት ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው ቁጥራቸውም በየአመቱ እያደገ ነው፡፡ በፓኪስታን ደግሞ 25 በመቶ ያህሉ ብቻ የስማርት ሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ቢሆኑም ቁጥሩ በየአመቱ በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ”12 ሚልዮን አርሶ አደሮች በሚኖሩባት ፓኪስታን 25 በመቶ ያህሉ የስማርት ሞባይል ስልክ ባለቤት የሆኑት እንኳን የሪከልት መተግበሪያዎችን ቢጠቀሙ 3 ሚልዮን የሚያህሉ አርሶ አደሮችን ተደራሽ ማድረግ ይቻላል” በቀጣይም በእርሻ ስራ የሚሰማራው ወጣት ትውልድ የኢንተርኔት ፣ የቲክቶክና የዩትዩብ ተጠቃሚ ስለሆነ የስማርት ሞባይል ስልክ ባለቤት የመሆን እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አስምሮበታል፡፡

ምንጭ፡- የዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS