ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአእምሯዊ ንብረት ምንነት፣ በሕግ ማዕቀፎችና በምዝገባ ስርዓት ዙሪያ ለክልልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች/ ኤጀንሲዎች/ባለስልጣን ባለሙያዎችለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀቀ፡፡

ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች፣ ኤጀንሲዎችና ባለስልጣን የተውጣጡ 36 .ባለሙያዎች በአእምሯዊ ንብረት ዙሪያ የተዘጋጀውን የአሰልጣኞች ስልጠና ተሳትፈዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት፣ የፓተንት፣ የንግድ ምልክትና የቅጅ መብት ጽንስ ሃሳብ፣ የምዝገባ ጠቀሜታ፣ የማመልከቻ አቀባበልና የመብት ጥሰት ተጠያቂነትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ  በሁለት ቀናት በነበረው መርሃ ግብር ተዳሰዋል፡፡

የክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች፣ ኤጀንሲዎችና ባለስልጣን  በየአካባቢያቸው የሚገኙ የአእምሯዊ ንብረት ውጤቶች ጥበቃ እንዲያገኙ፣ እንዲለሙና ወደ ገበያ እንዲገቡ ለማድረግ ከምክር አገልግሎት፣ ከማመልከቻ ቅበላና ከግንዛቤ ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተሰሩ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ናስር ኑሩ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማህበረሰቡንና የአካባቢውን ህዝብ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ ማሳደግ፣ የፈጠራ ባለመብቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፣ ከፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የህግ ማስከበር ስራዎች ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸት፣ የአእምሯዊ ንብረት ይዘት ያላቸውን ባለልዩ ጣዕምና ባህሪ ያላቸውን ምርቶች ከሚመለከታቸው የምርምር ተቋማት ጋር በመቀናጀት መለየትና የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እንዲያገኙ መስራት፣ የህብረት ስራ ማህበራትና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን መደገፍ  እንደሚጠበቅባቸው በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ  ላይ ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀረቡት የመወያያ ጽሁፎች መነሻነት በአእምሯዊ ንብረት ጽንስ ሃሳብና በየተቋሞቻቸው የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳት በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share this
CONTACT US

Email : info@eipa.gov.et
Address:

+251 115 52 80 00
+251 115 52 72 02
Fax:-  +251 115 52 92 99
Po.Box:- 25322/1000

USFULL LINKS